Back Save Expand Next

አራት ኪሎ አዲስ ብርሀን የገበያ ማዕከል አ.ማ B +G+9 የመኖሪያ ፣ የንግድ እና የቢሮ ህንፃ ላይ ካሉ ወለሎች መካከል 3ኛ ወለል በጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ይፈልጋል

Bids closing date 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
Bids opening date 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
Published on 2merkato.com ( የካቲት 12፣ 2013 )
Posted on የካቲት 12፣ 2013
Bid document price 200.00 ብር
Bid bond 2%

የጨረታ ማስታወቂያ

አራት ኪሎ አዲስ ብርሀን የገበያ ማዕከል አ.ማ በመመስረቻ ደንብ ቁጥር ቀ10/9355/44/2009 በተሰጠው ስልጣንና አባላቱ ጥር 05 ቀን 2013 ዓ.ም በወሰኑት ውሳኔ መሰረት በአራት ኪሎ ብርሀንና ሰላም ማተሚያ ፊት ለፊት ባስገነባው 2B +G+9 የመኖሪያ ፣ የንግድ እና የቢሮ ህንፃ ላይ ካሉ ወለሎች መካከል 3ኛ ወለል በጨረታ አወዳድሮ ለመስጠት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይፈልጋሉ፡፡

 • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ዋጋ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገኘው የካሬ ዋጋ ቦታ ትይዩ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ መሙላት ይገባቸዋል።
 • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ከኢማህበሩ የህንፃ አስተዳደር ቢሮ በግንባር በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
 • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውም እስከ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከፍት ሆኖ ከጠዋቱ 4፡30 ይዘጋል:: ጨረታው በዚሁ እለት ከረፋዱ 5፡00 ላይ ይከፈታል ።
 • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንዲሆን የመግዣውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው።
 • የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋ 50% ጨረታውን እንዳሸነፈ በተገለፀለት በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት፡፡ ቀሪውን 50% ደግሞ የመጀመሪያውን ክፍያ ከተከፈለበት ቀን ጀምሮ በ1 ወር ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ አለበት ፡፡
 • ክፍያው በተባለው ጊዜ ካልተከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው CPO ለአ.ማህበሩ ገቢ ይደረጋል፡፡ 
 • በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዙት ዋስትና ሲፒኦ ጨረታው ተጠናቆ ውጤቱ እንደታወቀ በ15 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይሆናል::
 • ለጨረታው የቀረበውን ቦታ (ወለል) ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 3 እስከ 11 እንዲሁም ቅዳሜ እስከ 6፡30 ድረስ በአካል በመምጣት መመልከት ይችላል ፡፡
 • አሸናፊው ተጫራች በንብረቱ ማስተላለፍ ሂደት ጊዜ ለመንግስት የሚከፈል ማንኛውም ክፍያ እና የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎችን አሸናፊው ተጫራች ይከፍላል ፡፡
 • አ.ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ሙሉ መብት አለው ::
 • ተጫራቶች ሌሎች ተጫራች ያቀረቡትን የጨረታ ዋጋ መነሻ በማድረግ ማቅረብ አይቻልም ::
 • ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢማህበሩ ህንፃ አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል ፡፡ ሙሉ ወለሉን ወይም 360 ካ.ሜ ቦታውን አጠቃሎ ለሚገዙ ተጫራቾች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
 • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0911223388 ወይም 0911654809 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ።

ተጫራቾች አንዲያውቁት

 • አ.ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ለጨረታ ያቀረበው ወለል (ቦታ) በሙሉ ለ5 ተከራዮች በማከራየት የ1አመት ውል ተዋውሏል፡፡
 • ከአምስቱ ተከራዮች የሚገኘው ወርሀዊ ቋሚ ገቢ 90,525.00 (ዘጠና ሺህ አምስት መቶ ሀያ አምስት ብር) ነው ይህ የኪራይ ገቢና የውል ስምምነት አሸናፊ ተጫራቹ የሚገዛበትን ሙሉ ክፍያ ከፍለው ካጠናቀቁበት ቀን ጀምሮ ወደ አሸናፊው ተጫራች የሚሸጋገር ይሆናል:
 • የጨረታው ሰነድ ተሞልቶ ሲገባ ኦርጅናል ማህተም ያረፈበት ብቻ ይሆናል ፡፡ በኮፒ የሚገባ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል ፡፡

አራት ኪሎ አዲስ ብርሀን የገበያ ማዕከል አ.ማ

 

 

Filed Under
Sales, Disposals and Foreclosure House and Building Sale
Sales, Disposals and Foreclosure House and Building Foreclosure

Exchange Rates

Selling
Buying
USD 40.7355 39.9368
GBP 55.0353 53.9562
EUR 49.5222 48.5512
CHF 42.8252 41.9855
CAD 29.3190 28.7441
AED 10.0356 9.8388
Source: Commercial Bank of Ethiopia
Applicable date: Feb 26th, 2021