Back Save Expand Next

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2012 በጀት ዓመት ለሆስቲታሉ መገልገያ የሚሆኑ ንብረቶችንና የተለያዩ አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

Bids closing date በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
Bids opening date በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
Published on 2merkato.com ( መስከረም 20፣ 2012 )
Posted on መስከረም 20፣ 2012
Bid document price Birr 100.00
Bid bond በየሎቱ የተለያየ ነዉ

የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር 01/2012 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2012 በጀት ዓመት በተያዘለት የመንግስት በጀት ለሆስፒታሉ መገልገያ የሚሆኑ

 • የደንብ ልብስና ለህሙማን መገልገያ አልባሳት፣
 • የጽህፈት መሳሪያዎች፣
 • የተለያዩ ሕትመቶች፣
 • የጽዳት እቃዎች፣
 • መድሃኒቶች እና የህክምና መርጃ መሳሪያዎች፤
 • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና፣
 • የሊፍት እና የጀነሬተር ጥገና፣
 • የህክምና መሳሪያዎች፣
 • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
 • ፈርኒቸሮች፣
 •  የተሟላ ስልጠና አዳራሽ ከመስተንግዶ አቅርቦት ጋር፣
 • የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት፣
 • የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ መስመር ድሬኔጅ በመስራት ከዋናው ሴፕቲክ ታንክ ጋር ማገናኘት ግንባታ አገልግሎት
 • የተሽከርካሪ መኪናዎች ጎማ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: 

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው የዋና ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው:: 

2. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩ የእቃ ወይም አገልግሎት አይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት የሚችሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ሎት (የጨረታ ሰነድ) የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በሆስፒታሉ የክፍያና ሂሳብ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሰነድ ሽያጭ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ይጠናቀቃል፡፡ 

3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

3.1. ለደንብ ልብስ እና ለህሙማን መገልገያ አልባሳት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00/ሃያ ሺ ብር/ 

3.2 ለጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 18,000.00 / አስራ ስምንት ሺ ብር /

3.3 ለተለያዩ ህትመቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ 

3.4 ለጽዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/አስር ሺ ብር/ 

3.5 ለመድሃኒቶች እና የህክምና መርጃ መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 /ስልሳ ሺ ብር/ 

3.6 ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00 / ስድስት ሺብር/ 

3.7 ለሊፍት ጥገና እና ጀነሬተር ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 8,000.00/ ስምንት ሺ ብር 

3.8 የተሽከርካሪዎች ጥገና አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00 / ስድስት ሺ ብር 

3.9 ለፈርኒቸር እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00/ሃያ ሺ ብር / 

3.10 ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺ ብር/ 

3.11 ለህክምና መሳሪያዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 /አርባ ሺ ብር/ 

3.12 ለስልጠና አዳራሽና መስተንግዶ አቅርቦት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00/ሁለት ሺ ር/

3.13 ልዩ ልዩ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 6,000.00 (ስድስት ሺ ብር) 

3.14 የተሽከርካሪ መኪናዎች ጎማ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4,000.00/አራት ሺ ብር/

3.15 የቢሮ ዉስጥ ለዉስጥ ጥገና እና የፍሰሽ መስመር ዝርጋታ ግንባታ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00(አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ተብሎ ማዘጋጀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ ብቻ በመሙላት የድርጅታቸውን ማኅተምና ፊርማ አኑረው ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ዘወትር በስራ ቀንና ሰአት ከጠዋቱ 2፡30-11:30 ሰዓት እንዲሁም በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የድርጅታቸውን ስም በማስመዝገብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: 

5. በተራ ቁጥር 4 ላይ ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ ለህክምና መሳሪያዎች ግዢ የጨረታ ሰነድ ውድድሩ በቅድሚያ ከቴክኒካል ሰነድ በመሆኑ ቴክኒካል ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ ፖስታ በማዘጋጀት ኦርጂናል ኮፒ በማለት እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ ፖስታ በማዘጋጀት ኦርጂናል ኮፒ በማለት በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

6. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም:: 

7. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ አዳራሽ ውሰጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አያግደውም፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ 

8. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ሳይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንዲሁም ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

9. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች ያለምንም አቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያነት አስይዞ ተገቢውን ውል በመፈጸም እቃዎቹን በሆስፒታሉ ግቢ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ እንዲሁም የአገልግሎትና ግንባታ ግዢዎችን በውሉ መሰረት በወቅቱ መፈጸም አለበት፡፡ 

10. ናሙና የሚቀርብባቸው የእቃ አይነቶች /የደንብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ተጫራቾች ለግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በማስፈረም የማስገባት ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ያልገባላቸው እቃዎች ዋጋ ስለሞሉ ብቻ ተወዳዳሪ አያደርጋቸውም፡፡ 

11. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል/የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 

አድራሻ፦ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር 

ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0114342330/0118-69-60-88/0911442730/ በስራ ሰአት መደወል ይችላል፡፡ 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል 

Company Info
Tirunesh Beijing General Hospital
Tirunesh Beijing General Hospital
ጥሩነሽ ቤጂንግ አጠቃላይ ሆስፒታል
Addressአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ወይም ልዩ ስሙ ጥምቀተ ባህር ወይም አቃቂ መሿለኪያ ፊት ለፊት
Phone+251 11 4342330
Phone2+251 118-69-60-88
Phone3+251 114342330
Filed Under
Construction and Water Works Sewerage
Advertising and Promotion Promotional Items
Advertising and Promotion Printed Advertising Materials
Office Supplies and Services Office Machines and Accessories
Health Care, Medical Industry Medical Equipment and Supplies
Maintenance and Repair Machinery
Maintenance and Repair Vehicle (garage service)
Health Care, Medical Industry Health Related Services and Materials
Furniture and Furnishing House Furniture
Furniture and Furnishing Office Furniture
IT and Telecom Computer and Accessories
Electrical, Electromechanical and Electronics Installation, Maintenance and Other Engineering Services
Electrical, Electromechanical and Electronics Equipment and Accessories
Energy, Power and Electricity Generators
Hospitality, Tour and Travel Hotel Service Provision
Construction and Water Works Road and Bridge Construction
Health Care, Medical Industry Pharmaceutical Products
Maintenance and Repair Office Machines and Computers
Office Supplies and Services Stationery
Construction and Water Works Water Construction
Textile, Garment and Leather Shoes and Other Leather Products
Textile, Garment and Leather Textile, Garments and Uniforms

Exchange Rates

Selling
Buying
USD 34.9029 34.2185
GBP 41.2853 40.4758
EUR 38.7736 38.0133
CHF 34.6705 33.9907
CAD 23.0327 22.5811
AED 8.5987 8.4301
Source: Commercial Bank of Ethiopia
Applicable date: Jun 2nd, 2020