ኢትዮ ቴሌኮም ለኩባንያው አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያየ ዓይነት ሞዴል ያላቸው ኘሪንተሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Print

Bid closing date
May 29, 2023 5:00 PM
Bid opening date
May 30, 2023 10:00 AM
Published on
ethiotelecom (May 10, 2023)
Posted
Bid document price
100.00 (አንድ መቶ ብር)
Bid bond
5%
Region

ጨረታ ቁጥር፡ SC/L/WRM/004/2015

 

የጨረታ ቁጥር

የጨረታው ሰነድ ሽያጭ የሚጀምርበት ቀን

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

SC/L/WRM/004/2015

ግንቦት 5/2015

ግንቦት 21 ከቀኑ 11:3ዐ

ግንቦት 22 ቀን ከጠዋቱ 4፡00

ኢትዮ ቴሌኮም ለኩባንያው አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያየ ዓይነት ሞዴል ያላቸው ኘሪንተሮችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርቦ መወዳደር ይችላል።

1.   ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ. ም እስከ ግንቦት 21 ቀን 2015 . ድረስ ባሉት ቀናት www.2merkato.com, www.afrotender.com: www.extratenders.com ዌብ ሳይቶች በመግባትና በቴሌ ብር አማካኝነት የማይመለስ ብር 100.00 (ብር አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በማንኛውም ጊዜና ሰዓት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ስማቸውን፣ የድርጅታቸውን ስምና የስልክ ቁጥር መመዝገባቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡

2.   ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውጤቱ እንደታወቀ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና አገልግሎት ላይ ያልዋሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ኘሪንተሮች ለመግዛት የሚያቀርቡበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3.   የጨረታ ማስከበሪያው ዋስትና ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ብቻ ለሚጫረቱበት እቃ በተናጠል መቅረብ አለበት፡፡

4.   ተጫራቾች በተጠቀሱት ዌብ ሳይቶች የጨረታ ሠነዱን ግዥ ከፈፀሙ በኋላ የታደሰ መታወቂያቸውን በመያዝ ከግንቦት 5 ቀን 2015 እስከ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለጨረታ የቀረቡትን  ኘሪንተሮች ሄደው መመልከት ይችላሉ፡፡

5.   ተጫራቶች የታደሰ ንግድ ፍቃዳቸውን እና ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ቫትን (VAT) ጨምረውዋጋ ማስገቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዱን (CPO) በማካተት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን እና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ በኢትዮ ቴሌኮም አቃቂ ዕ/ግ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘገጀው ሳጥን እስከ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6.   ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮ ቴሌኮም አቃቂ ዕ/ግ/ቤት ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጨራቾች ብዛት ታይቶ የጨረታ መክፈቻ ቦታ ሊቀየር ይችላል፡፡ ተጫራቾች በጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

7.   ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ አቃቂ ዕቃ ግምጃ ቤት (ወደ አዳማ በሚወስደው አዲሱ መንገድ ላይ) በሚገኘው በኢትዮ ቴሌኮም ዋናው ዕቃ ግምጃ ቤት ቢሮ ቁጥር ዐ1 በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል ፡፡

ክፍል አንድ

1.  ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች

1.1  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.1.1    ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት የጨረታ ሰነዱን ከተጠቀሱት ዌብ ሳይቶች በመግዛት ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

1.1.2    ለጨረታው ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ C.P.O. ቼክ ለእያንዳንዱ ለሚጫረቱበት እቃ በተናጠል ማስገባት አለባቸው፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያላቀረበ ተጫራች ጨረታው በሚከፈትበት ወቅት ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡

1.1.3    ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ከታች በተ.ቁ. 3.1 ላይ በተጠቀሰው አድራሸ የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

1.1.4  ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው ከተከፈተበት ዕለት አንስቶ ለ90 ቀን የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡

1.1.5    ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለጨረታው ያቀረቡትን ዋጋ ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል መጠየቅ አይችሉም፡፡

1.1.6  ጨረታው ተከፍቶ ውጤቱ እስከሚታወቅ ተጫራቾች ውድድሩን መተው አይችሉም፡፡ የጨረታው ውጤት ሳይታወቅ ውድድሩን መቋረጥ የሚፈልግ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይደረጋል፡፡

1.1.7    ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የጨረታ ሰነድ ማቅረብ አይቻልም፡፡

1.1.8    አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

2.  የጨረታ ሰነድ አዘገጃጀት

2.1    ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሰነዱ የሚጠይቃቸውን መረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

2.2    ተጫራቾች የሚገዟቸውን የተለያዩ ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ እቃዎችን በዝርዝር በመለየት ለእያንዳንዱ እቃ ዋጋ በነጠላ እና በድምር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2.3    ተጫራቾች የታደሰ መታወቂያቸውን በመያዝ መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በሚገኙበት ቦታ ማለትም መስቀል ፍላወር በሚገኘው የድርጅቱ ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት እስከ ግንቦት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

2.4    ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡት ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ ሰነዳቸው ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ከሆነ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሉ በተሰረዘው ቦታ ላይ መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡

2.5    ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጓቸውን የተለያዩ ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና አገልግሎት ላይ ያልዋሉ ፕሪንተሮችን በተዘጋጀላቸው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዋጋቸውን በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲፒኦ ጋር በታሸገ ፖለስታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚሰጡት ዋጋ ሳንቲም የሚኖረው ከሆነ ሳንቲሙ በነጥብ መለየት ይኖርበታል፡፡

2.6    ተጫራቾች ለጨረታው የሚያቀርቡት ዋጋ የሚያቀርቡትን የእያንዳነዱን ዋጋ ብግልጽ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡

2.7    ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ሲፒኦ ለሚጫረቱበት ዕቃአይነት በተናጠል ወይም በጥቅል 5% ማስያዝ አለባቸዉ፡፡

2.8    ተጫራቾች እቃዎችን ለማየት በሚመጡበት ግዜ ማናቸውንም አይነት የልኬት መሳሪያዎች ይዘው መምጣት የተከለከለ ነው፡፡ በተጨማሪም ከተቀመጡ ሳምፕል ውጪ ማየት የተከለከለ ነው፡፡

2.9    አሸናፊው አካል በጨረታው ያሸነፋቸውን እቃዎች በሚያነሳበት ወቅት መምረጥ አና መርጦ /መርጣ/ መተው አይችልም፡፡ ጨረታው በወጣው ምድብ መሰረት ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ድርጅቱ እንዲነሳለት ባስቀመጠው ምድብ ተራ. ቁጥር እንዲያነሳ ይገደዳል፡፡ ተ.ቁጥሩን ድርጅቱ ያሳውቃል፡፡ እቃው ባለበት በጉልህ በሚታይ ቦታ ይለጠፋል፡፡

2.10  አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የሚመለስላቸው ላሸነፋበት ዕቃ ሙሉ ክፍያውን ከፍለው እቃውን ሙሉ በሙሉ ማንሳታቸው ሲረጋገጥ ብቻ ነው፡፡ ዕቃው ሙሉ በሙሉ ካላነሱ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ይወረሳል፡፡

3.  የጨረታ አቀራረብ

3.1    ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው መመሪያ መሰረት ያዘጋጁትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ስልክ ቁጥሮቻቸውን እንዲሁም የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ በአቃቂ ዕ/ግ/ቤት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ የተቀባይ አድራሻ በሚከተለው ሁኔታ መጻፍ ይኖርበታል፡፡

ለኢትዮ ቴሌኮም

ሰፕላይ ቼይን ዲቪዥን

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡ SC/L/WRM/004/2015

የፖስታ ሳጥን ቁጥር 1047

አዲስ አበባ

 ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ስለመልቀቅ

4.1.   አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው ውል ፈርሞ ላሸነፈበት ዕቃ ክፍያ ከፈጸመ እና የተከፈለበት ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡

4.2.   በጨረታው ሁለተኛ የወጣው ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚደረገው አንደኛ የወጣው ተጫራች ሙሉ ክፍያውን መክፈሉ ከተረጋገጠ በኋላ ይሆናል፡፡

4.3.   ሌሎች ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው ሽያጭ ውሳኔ እንዳገኘ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

4.4.   ከአንድ በላይ ለሆኑ መደቦች (ካታጎሪ) በአንድ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ላቀረበ ተጫራች ከላይ በቁጥር 4.1 – 4.3 የተቀመጡት መመሪያዎች ተፈጻሚ ይደረጋሉ፡፡

5.  ግብር፣ ታክስና ሌሎች ወጪዎች አከፋፈል ሁኔታ

5.1    ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ቀደም ሲል የሚፈለግ የመንግስት ግብር ወይም ቀረጥ ካለ ኢትዮ ቴሌኮም ሙሉ ወጪውን ይከፍላል፡፡

5.2    አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ሰራተኞች እና ወጪ ያነሳል፡፡

5.3    ኢትዮ ቴሌኮም ከሽያጩ ጋር በተያያዘ የድጋፍ ደብዳቤዎች ለሚመለከተው የመንግስት አካል ይጽፋል፡፡

 

6.  የውል አፈጻጸም

6.1  መስሪያ ቤቱ ግምገማው ከተጠናቀቀ በኋላ ለአሸናፊው ተጫራች የአሸናፊነት ደብዳቤ /Award Letter/ ያዘጋጃል፡፡

6.2  መስሪያ ቤቱ ከአሸናፊነት ደብዳቤ /Award Letter/ ጋር ረቂቅ ውል አዘጋጅቶ ለአሸናፊው ያቀርባል፡፡

 

6.3  አሸናፊው በማሸነፊያ ደብዳቤ ላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ በጨረታው ያሸነፈባቸውን ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ የተለያዩ ዕቃዎች ሙሉ ክፍያ ፈጽሞ ውል በመፈራረም በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል፡፡

6.1  አሸናፊው ከላይ በተ.ቁ 6.3 ላይ በተጠቀሰው መሰረት ባይፈጽም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተወርሶ ሁለተኛ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡

 

ክፍል ሁለት

2.1 አገልግሎት ላይ ያልዋሉ አዳዲስ ኘሪንተሮች ዝርዝር ዋጋ ማቅረቢያ እና የሚገኙበት ቦታ

ምድብ

የዕቃዎቹ አይነት

መለኪያ

የዕቃዎቹ ብዛት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ያንዱ ዋጋ

ጠቅላላ ዋጋ

ዕቃዎቹ የሚገኙበት ቦታ

1

Samsung M288x Series Printers

በቁጥር

180

 

5,350

 

 

መስቀል ፍላወር የሚገኘው ዋ/ዕ/ግምጃ ቤት

2

Kyocera ECOSYS M2640idw Printers

በቁጥር

2170

 

8,850

 

 

መስቀል ፍላወር የሚገኘው ዋ/ዕ/ግምጃ ቤት

 

2.2. ገዢ ማንኛውንም ክፍያ የሚፈፅመው በሻጭ ስም (ኢትዮ ቴሌኮም) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ የባንክ ሂሰብ ቁጥር 1000000888757 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ለማቅረብ ተስማምቷል፡፡

ክፍል ሦስት

በተጫራቾች የሚሞላ

. አድራሻ መግለጫ ቅጽ

1.የተጫራቹወይምየተወካዩ   ስም__________________________________________

  2. ቋሚ አድራሻ

ከተማ________ /ከተማ________ ቀበሌ_________ የቤ._______________

3.   የቤት ስልክ________________ሞባይል ቁጥር _____________ ፋክስ ቁጥር ___________

 

   ፊርማ __________________

 

   ቀን ____________________

 

   ማህተም፡-

 

ማሳሰቢያ፡-

·   ማንኛውም ተጫራች ከላይ በቀረበው ፎርም መሰረት መረጃዎችን ሙሉ በሙሉ በመሙላት ፊርማ/ማህተም ማኖር ይጠበቅበታል፡፡

·       ይህንን ፎርም ለጨረታ ከሚያቀርቡት ዝርዝር ጋር አብረው ማቅረብዎትን አይዘንጉ፡፡

 

 

Company Info
Filed Under