ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል
Tender Documents
የጨረታ ማስታወቂያ
ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግል ማኅበር በተለያዩ የንግድ ሥራ ዘርፎች ማለትም በኮንስትራክሽን፣ እርሻ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ኢምፖርት-ኤክስፖርት፣ ማእድን፣ እና ሌሎች መሰል ዘርፎች ላይ የተሰማራ ግዙፍ የግል ንግድ ተቋም ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱም አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አዲሱ ገበያ ፖላንድ ኤምባሲ አጠገብ ይገኛል፡፡ በዚሁ በተጠቀሰው አድራሻ ከሳሬም ኢንተርናሽል ሆቴል ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው ዋናው አስፋልት ጎዳና ዳር ከመስቀለኛው ተሸግሮ ከሸገር መናፈሻ ዝቅ ብሎ ፖላንድ ኢምባሲ ጎን የሚገኘውን ባለ 5 ወለል ሙሉ ሕንጻ በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡
የሕንጻው ጠቅላላ ሁኔታ
በጨረታ ለኪራይ የቀረበው ሕንጻ ለንግድ ምቹ በሆነ አካባቢ የሚገኝ፣ ከፖላንድ ኢምባሲ ጋር በአጥር የተጎዳኘ፣በዋናው አስፋልት ጎዳና አንጻር የምድር ወለሉን አራት የተለያዩ ባንኮች ተከራይተው የሚሰሩበት፣ ለጥበቃ ምቹ የሆነ የተሟላ አጥር ቅጥር ያለው፣ ለኃይል መጠባበቂያ ጀኔሬተር ማስቀመጪያ የተደላደለ ቦታ ያለው፣ በግቢው እና ከግቢው ውጪ በቂ የሆነ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው፣ የዉሃ ማጠራቀሚያ ሮቶዎች ማስቀመጪያ በቂ ቦታ ያለው፣ በየወለሉ በቂ የመጸዳጃ ክፍሎች ያሉት ዘመናዊ ሕንጻ ሲሆን ሕንጻው ለባንኮች ከተከራየው ክፍሎቹ በስተቀር በሙሉ እና በአንድ ጊዜ ለአንድ ተጫራች የሚከራይ ይሆናል፡፡
የህንፃውን ምስል ለመመልከት ከዚህ በታች የተቀመጠው ሊንክ ይጫኑ።
https://tender.2merkato.com/tender-documents/640b3c81a1b34c3423691161
በመሆኑም ህጋዊ ፈቃድ ያላችሁ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተከራይ ድርጅቶች እስከ መጋቢት 12 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ በድርጅታችን በአካል በመገኘት የድርጅታችሁን የሥራ ፈቃድ፣ ቲን፣ ቫት፣ እና ተያያዥ ሰነዶች ከዚህ በታች በተመለከተው አድራሻ በአካል በመገኘት የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ የምትከራዩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
ተጫራቾች የቢሮዎቹን ሁኔታ ከሰኞ እስከ ዓርብ ዘወትር በስራ ሠዓት በአካል ተገኝተው መጎብኘት ይችላሉ፡፡
ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃላ.የተ.የግል ማህበር
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ከሰሜን ማዘጋጃ ከፍ ብሎ ፖላንድ ኢምባሲ አጠገብ
ቤአኤካ ሕንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 አስተዳደር መምሪያ
ስልክ ቁጥር 0911256371 ወይም 0930006336