ኬር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ  በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቅምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለቡት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Print

Bid closing date
Feb 03, 2023 12:30 PM
Bid opening date
Feb 03, 2023 2:00 PM
Published on
ቱመርካቶ.ኮም (Jan 18, 2023)
Posted
Bid document price
300 ብር
Bid bond
20%
Region

የጨረታ ማስታወቂያ

ኬር ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ  በጎ አድራጎት ድርጅት ሲጠቅምባቸው የነበሩ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባለቡት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

ተጫራቾች

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተሽከርካሪዎቹ  በሚገኙበት አድራሻ  በአዳማ ኬር ኢትዮጵያ ወደ ሶደሬ መንገድ ጥቁር አባይ ሆቴል ፊትለፊት ባለው TAF ማደያ አለፍ ብሎ በሚያስገባው የኮብል ስቶን ንጣፍ መንገድ 500 ሜትር ገባ ብሎ  ባለው የመጋዘን  ቢሮ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰአት ድረስ መመልከት ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት  ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%)  የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ /Column/ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቬሎፕ/ፓስታ/ በአዲስ አበባ፡ ኬር ኢትዮጵያ ሃያ ሁለት ማዞሪያ መንገድ፡ ከሌክስ ፕላዛ ጀርባ  ወደ አድዋ ድልድይ   በሚወስደው መንገድ ሁለተኛ ቅያስ ሁለተኛ ፎቅ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታውን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን በሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በአፍሮ ቴንደር፡ 2መርካቶ እና ሪፖርተር  ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ  የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውሰጥ ተሽከርካሪዎችን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች  የተሽከርካሪዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) እየከፈሉ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከተታይ የሥራ ቀናት ከአፍሮ ቴንደር መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. የጨረታ መዝጊያ ቀን ጥር 26 2015 ዐ.ም ከቀኑ 6፡30 ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡00 ሰኣት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ሃያ ሁለት መንገድ ከሌክስ ፕላዛ ጀርባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሰባት ቀበሌ 11/12 በሚገኘው  የ ቀበሌው አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ
  10. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

NOTE: A complete set of bidding document shall be obtained from Afrotender.com with nonrefundable fee of birr 300 (Three Hundred) from January 18th, 2023:    

ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስልክ ቁጥር 0116183294 ፣ 0923084216 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ኬር ኢትዮጵያ 

 

Company Info
Filed Under