ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Tender Documents
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከመስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቱመርካቶ ዶት ኮም (tender.2Merkato.com) ፣ ከኤክስትራ ቴንደር (extra tender) ፣ እና አፍሮ ቴንደር (afro tender) ዌብ ሳይት በመግባት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
2. ተሽከርካሪዎቹን ለማየት ተጫራቾች መታወቂያቸውን በመያዝ አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከመስከረም 23 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ማየት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በመዝጊያው ቀን ጥቅምት 22 እስከ ጠዋት 6፡30 ድረስ ብቻ ይሆናል።
3. ጨረታ የሚዘገው በጥቅምት 22 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ነው።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አቃቂ በሚገኘዉ የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ይከፈታል።
5. ኢትዮ ቴሌኮም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
6. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
Company Info

Ethio Telecom
ኢትዮ ቴሌኮም
Address | addis ababa |
---|---|
Website | http://www.ethiotelecom.et |