በጭዋኔ አስመጭና ላኪ ኃ/የተ/የግል ማህበር የማርዳ ቀለምና እምነበረድ ፋብሪካ አነስተኛ ሳይዝ (Under Size) ያላቸውን የወለል ምንጣፍ እምነበረድ እቃዎችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


Print

Bid closing date
በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
Bid opening date
በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
Published on
ቱመርካቶ.ኮም (Jun 16, 2022)
Posted
Bid document price
100.00 (አንድ መቶ ብር)
Bid bond
1%
Region

አነስተኛ ሳይዝ (Under Size) የወለል ምንጣፍ እምነበረድ ሽያጭ 

የጨረታ ማስታወቂያ

በጭዋኔ አስመጭና ላኪ ኃ/የተ/የግል ማህበር የማርዳ ቀለምና እምነበረድ ፋብሪካ አነስተኛ ሳይዝ (Under Size) ያላቸውን የወለል ምንጣፍ እምነበረድ እቃዎችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም

  1. የጨረታ ሰነዱን ሽያጭ ለሁሉም ተጫራቾች ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 አዲስ አበባ መውጫ  በፋብሪካው ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘዉ ዋና መስሪያ ቤታችን ፒያሳ ፤ ቸርችል መንገድ በሚገኘዉ እሸቱ ማሞ ኮሜርሻል ቢሮ ቁጥር 805 በመገኘት ለ10 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /መቶ ብር/ ከፍሎ መውሰድ ይቻላል።
  2. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን እስከ 10 ቀን ሆኖ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ  ባህርዳር በሚገኘዉ ፋብሪካችን ቢሮ ድረስ በመምጣት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማሳዣ /cpo/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4.  ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፋብሪካው ቢሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ታሽጎ ይከፈታል።
  5. ማርዳ ቀለምና እምነበረድ ፋብሪካ በጨረታው ላይ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ከጨረታ በኋላ አሸናፊው እቃዎችን ርክክብ በሚደረግበትም ሆነ ከሌላ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ምክንያት የሚከሰቱ ወጪዎች ካሉ ገዥ ይሸፍናል።
  7.  ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 096 145 4545 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
Company Info
Filed Under