ብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ቢሮውን ለማደስ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
ብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ
የቢሮ እድሳት ለማድረግ የወጣ የጨረታ ማስታወቅያ
ድርጅታችን ብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ ቢሮውን ለማደስ አስፈላጊ ሆኖ በማግኘቱ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁና ፍላጎቱ ያላችሁ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ከዋናው መስሪያ ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር መምሪያ በማቅረብ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ከፍሎ በመግዛት ስራውን የምትሰሩበትን ዋጋ ከተገቢ ህጋዊ ሰነዶች/ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል/ ጋር በተለያየ የታሸገ ፖስታ በማቅረብ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- የ2012 ዓ/ም ግብር የከፈሉ ተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና ሌሎች ተያያዥ ህጋዊ ሰነዶችን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን 2 በመቶ ቢድ ቦንድ ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ስራ ለመስራታቸውና በቂ አቅምና ልምዱ ያላቸውን መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል::
ተጫራጮቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን ጨረታው ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ/ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች በሙሉ አሟልተው የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ አለው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251930020395 በመደወል ይጠይቁ፡፡
ብሬክስሩ ትሬዲንግ አ.ማ
በዚህም መሰረት የሚሰሩ ስራዎችን በሄልዘር ታወር ሶስተኛ ፎቅ በመቅረብ ዝርዘር መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
About the Company
Helther Tower, 3rd floor, around Bole Medhanialem in front of Sheger House
