ወደኋላ ይቀመጥ ማስፊያ ቀጣይ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በቤት ግንባታ ላይ የተሠማሩ ተቋራጮችን የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ለመገንባት የሚያስችል የጽንሰ ሀሳብ ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ ይጋብዛል

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን Jun 15, 2021 10:00 AM
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የጨረታው መክፈቻ ቀን አልተገለጸም
የታተመበት ጋዜጣ 2merkato.com ( ግንቦት 18፣ 2013 )
የተለጠፈበት ቀን ግንቦት 18፣ 2013

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

Federal Democratic Republic of Ethiopia

OFFICE OF THE PRIME MINISTER

የመኖሪያ አፓርትመንቶች ግንባታ ፕሮፖዛል ጥሪ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የራሱን ፕሮጀክት ለመከወን የሚያስችለውን ቦታ ከኦሮሚያ ልዩ ዞን የተረከበ ሲሆን፣ ከመካከሉ የተወሰኑትን በቤት ግንባታ ላይ በተሠማሩ ተቋራጮች ለማሰራት አቅዷል።

በዚህም መሠረት፣ ጽሕፈት ቤቱ በቤት ግንባታ ላይ የተሠማሩ ተቋራጮች የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ለመገንባት የሚያስችል የጽንሰ ሀሳብ ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፦

  1. የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተረከበው ይዞታ ላይ በከፍተኛ ጥራት እና ዓለም አቀፍ ደረጃን በጠበቀ መልኩ የሚለማ እና አስፈላጊውም መገልገያ ያሟላ አዲስ የከተማ መንደር ለማልማት አቅዷል።
  2. በራሳቸው አቅም 10,000 (አስር ሺህ) የሚበልጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን ለመገንባት የሚችሉ ተቋራጮችን ይጋብዛል። ለልማት የተመረጠው ስፍራ ባለ ፎቅ ሕንጻዎችን እና ተያያዥ መገልገያዎችን እንዲያካትት ታስቧል።
  3. ሥራውን የሚከውነው ተቋራጭ መኖሪያ አፓርትመንቶችን ሲገነባ፣ ፎቅ ሕንጻዎችን በብሎክ የሚገነባ ይሆናል።

ይህንን ሥራ ለመከወን አስተማማኝ የገንዘብ አቅም እና ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያላቸው በቤት ግንባታ ላይ የተሠማሩ ተቋራጮች info@pmo.gov.et  ወይም +251-111241224 ወደ ጽሕፈት ቤቱ በመደወል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይችላሉ።

የጽንሰ ሀሳብ ፕሮፖዛሉየከተማ መንደር ግንባታ የጽንሰ ሀሳብ ፕሮፖዛልየሚል ርዕስ በተጻፈበት እና የጽሕፈት ቤቱን አድራሻ ባከተተ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 8 2013 .. ከጠዋቱ 400 ድረስ ባሉት ቀናት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እንግዳ መቀበያ በአካል በመቅረብ የሚገባ ይሆናል። 

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የቀረቡ ፕሮፖዛሎችን በሙሉም ሆነ በከፊል የመቀበል ወይም የመተው መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮጵያ: አዲሲቷ የተስፋ አድማስ

Ethiopia: A New Horizon of Hope

Filed Under
Construction and Water Works Building Construction
Construction and Water Works Contract Administration and Supervision

የምንዛሬ ዋጋ

መሸጫ
መግዣ
USD 44.4268 43.5557
GBP 58.9149 57.7597
EUR 52.8502 51.8139
CHF 46.0970 45.1931
CAD 32.4636 31.8271
AED 10.9346 10.7300
ምንጭ: Commercial Bank of Ethiopia
የሚተገበርበት ቀን: Jun 23rd, 2021