ወደኋላ ይቀመጥ ማስፊያ ቀጣይ

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ. የግል ማህበር የዳታ ሴንተር ለማደራጀት ያስችለው ዘንድ ለዚህ ተግባር የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ15ኛው ቀን ማለትም እ.አ.አ. በ25/09/2019 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
የታተመበት ጋዜጣ 2merkato.com (Sep 11, 2019)
የተለጠፈበት ቀን Sep 11, 2019

የጨረታ ማስታወቂያ

  1. አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ. የግል ማህበር የዳታ ሴንተር ለማደራጀት ያስችለው ዘንድ ለዚህ ተግባር የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፤  
  2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ሕጋዊ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም በጨረታው ለመሳተፍ የሚያበቃ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የግብር ክሊራንስ ስልጣን ካለው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በገዥ አድራሻ ማለትም አ/አበባ ከተማ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር አዲስ ኢትዮ-ቻይና መንገድ (በተለምዶ ወሎ ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ) አምባስል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ መታወቂያ ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የብቃት ማረጋገጫ ኮፒውን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ ተወካዮች ከሆኑ ሕጋዊ የውክልና ሰነዳቸውን ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ከታወጀበት/ከወጣበት እ.አ.አ. ከ11/09/2019 ወይም ከ06/13/2011 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን ማለትም እ.አ.አ. በ25/09/2019 ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በአገልግሎት ገዥ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ማለትም አምባሰል ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ላይ የጨረታ መከፈት ስነ- ስርዓቱን መከታተል የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚታሸግበት እንዲሁም (ወይም) ጨረታው የሚከፈትበት ቀናት ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በአላት ከሆኑ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀናት የሚከናዎን ይሆናል፡፡ በጨረታ መክፍት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታውን ዋጋ አያሳጣውም፡፡
  6. ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

ስልክ ቁጥር - 0114700350 /0114666239/ 0114666802 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይቻላል፤

አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር

 

Company Info
Ambasel Trading House PLC
Ambasel Trading House PLC
አምባሰል የንግድ ሥራዎች ኃ.የተ.የግል ማህበር
AddressWolo Sefer - Ethio-China friendship road, Ambasel building 4th-floor office No. 406.
Phone0114700350
Phone20114666239
Websitehttp://www.ambaseltrading.com.et
Filed Under

የምንዛሬ ዋጋ

መሸጫ
መግዣ
USD 29.9224 29.3357
GBP 34.9969 34.3107
EUR 32.9955 32.3485
CHF 28.7860 28.2216
CAD 20.3439 19.9450
AED 7.3725 7.2279
ምንጭ: Commercial Bank of Ethiopia
የሚተገበርበት ቀን: Oct 12th, 2019